input
stringlengths
1
130k
ምክንያቱ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በአብዛኛዉ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተዋል ድምፅ ቆጠራዉም በአመዛኙ ግልፅ ነበር ሲሉ እማኝነታቸዉን ሰጥተዋል።
የአፍሪቃ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንም የአዉሮጳ ኅብረት ታዛቢ ቡድን የሰጠዉን አስተያየትና ትዝብት እንደሚጋራ አስታዉቋል።
የሀገሪቱ የተቃዉሞ ፖለቲካ አባላትና ደጋፊዎች ግን ምርጫዉ ተጭበርብሯል ተቀባይነት የለዉም እያሉ ነዉ።
የቻተም ሃዉሱ የፖለቲካ ተንታኝ ፖል ሜሊ ተቃዋሚዎቹ አጠቃላይ የምርጫዉ ዉጤት ከመነገሩ አስቀድመዉ ተጭበርብሯል በሚል ያወገዙበት ምክንያት ታሪካዊ ይዘት አለዉ ይላሉ።
ስለዚህ በተቋማቱ ላይ እምነት ለማሳደር ሂደቱ በጣም አዝጋሚ ነዉ።
ፕሬዝደንት አልፋ ኮንዴ በዚህም ላይ ይላሉ ሜሊ ፕሬዝደንት ኮንዴ ራሳቸዉ ነገሮችን አቻችሎ ለመስማማት ከመቅረብ ይልቅ ጫና የሚያደርጉም ይመስላል።
የዛሬ አምስት ዓመት ከተመረጡ በኋላም መድበለ ፓርቲን የሚፈቅዱ ዓይነትም አልሆኑም።
ምንም እንኳን የምርጫዉ ታዛቢዎች ሂደቱን ተከታትለዉ አስተያየታቸዉን ቢሰጡም እንደፖል ሜሊ አባባል ምርጫ ላይ የሚፈፀመዉ ጫና አስቀድሞ የሚከናወን ነዉ።
የፖለቲካ ተሳታፊና እጩዎች ማግኘት የሚገባቸዉ መገናኛ ብዙሃንን መጠቀምን በተመለከተም ስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝደንት አልፋ ኮንዴ በጣም ሰፊና ጠንካራ ሽፋን ተሰጥቷቸዋል።
የምርጫ ታዛቢዎችም ተቃዋሚዎች ምርጫዉ ተጭበርብሯል ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ ወደጎን በማድረግ ተዓማኒ እንደሆነ ገልጸዋል።
የተቃዉሞ ፖለቲከኛዉ ሴሉ ዳሊን ዲያዮ በሌላ በኩል ግን ምናልባት የመለያ ምርጫ ሊካሄድ ይችል ልሆናል የሚል ግምት አለ።
አጠቃላይ ዉጤቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት የቀረበዉ የታዛቢዎቹ አስተያየት ተፅዕኖ ማስከተሉ እንደማይቀር ሜሊ ይናገራሉ።
ድጋሚ ምርጫ ማካሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ ዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች አንሳተፍም ለማለት አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል።
አልፋ ኮንዴን ድጋሚ ለመፎካከር አንሳተፍም ካሉ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ እንደሌላቸዉ ያዉቃሉ።
ሚሊዮን ሕዝብ እንዳላት የሚነርላት ጊኒ ከአንድ ዓመት በላይ በምዕራብ አፍሪቃ በኤቦላ ተሐዋሲ ክፉኛ ከተጎዱ ሃገራት አንዷ ናት።
በዚሁ መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሚሆኑ የመጀመሪያዎቹ ስደተኞችም እስከ ፊታችን ጥር አጋማሽ ኢጣልያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ስደተኞችን ወደ ኢጣልያ መምጣት የሚያስችላቸው ሰብዓዊ ቪዛ የሚያገኙባቸውን ቢሮዎች በሞሮኮ በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ ለመክፈት አቅደዋል ።
የስደተኞቹን የጉዞ የመስተንግዶ እና የቋንቋ ትምህርት ወጪ እንዲሁም ለተገን ጥያቄአቸው የሚያስፈልጋቸውን ህጋዊ ድጋፍ ድርጅቶቹ እንደሚሸፍኑም ተዘግቧል ።
የሮሙን ወኪላችንን ተክለ እግዚ ገብረ እየሱስን ስለ እቅዱ አተገባበር ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ጠይቄዋለሁ ።
ኤኮኖሚ የፊናንሱ ቀውስ የመፍትሄው ጥረትና ታዳጊው ዓለም የዓለም ኤኮኖሚ ከመቼውም በላይ እየተሳሰረ መሄድ ከጀመረ ሰንበት ያለ ጉዳይ ነው።
ለነገሩ የዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ሰለባ ዛሬ የበለጸገው ዓለም ብቻ አይደለም።
በተናጠል በብሄራዊ ደረጃ በሚራመድ ዕቅድ ዓለምአቀፍ የሆነ ችግርን ለመፍታት መቻሉም ሲበዛ ያጠያይቃል።
ታዲያ በወቅቱ ሂደት ታዳጊ አገሮች እንደገና ተጎጂዎቹ እንዳይሆኑ የሚሰጉት የኤኮኖሚ ጥበብት ጥቂቶች አይደሉም።
ዓለምአቀፉን የፊናንስ ቀውስ ለመታገል ካለፈው ሕዳር ወር ወዲህ እስካሁን በአውሮፓና በአሜሪካ የፈሰሰው ገንዘብ በብዙ ሚሊያርድ ዶላር የሚቆጠር ነው።
የፊናንሱ ቀውስ አምራቹን ኤኮኖሚም ችግር ላይ መጣሉ ጎልቶ በተከሰተበት በአዲሱ ዓመትም መንገዳገድ የያዙ ባንኮችንና ኩባንያዎችን ለማዳን ሰፊ በጀት ማፍሰሱ ቀጥሏል።
ማገገሚያው ዕቅድ የዓለምአቀፉን የፊናንስ ገበዮች ችግር ለማሸነፍ በሚበጅ መንገድ ተቀናጅቷል ለማለት አይቻልም።
ይሁንና እያደር የአውሮፓ የፊናንስና የኢንዱስትሪ ዘርፎችም በወቅቱ የችግሩ ተጽዕኖ እየተሰማቸው መሄድ ይዟል።
የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪው በፊናንሱ ቀውስ የተነሣ በተከሰተው የፍላጎት መቀነስ ሳቢያ ምርቶቹን እንደቀድሞው ገበያ ላይ ሊያውል አልቻለም።
ለዚሁ የኢንዱስትሪ ዘርፍ መለዋወጫ ዕቃ የሚያመርቱ በሺህ የሚቆጠሩ ኩባንያዎችም ሠራተኛ ወይም የምርት ሰዓት እስከመቀነስ ደርሰዋል።
ይህም ከአገሪቱ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት አንጻር ከመቶው መሆኑ ነው።
የሚቀጥለው ዓ ም የበጀት ኪሣራ እንዲያውም ወደ አራት ከመቶ ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ።
ችግሩ ጠንከር ያለ ዕርምጃን የሚጠይቅ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም።
የአገሪቱ ጥምር መንግሥት ባለፈው ሰኞ የተስማማበትን ሰፊ የኤኮኖሚ ማነቃቂያ ዕቅዱን በፍጥነት ገቢር ለማስደረግ ሲጥር መሰንበቱም የጉዳዩን ክብደት የሚያሳይ ነው።
የበርሊኑ ካቢኔ በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ከመከረ በኋላ ቻንስለር እንጌላ ሜርክልም ዕቅዳቸውን ለም ቤት አብራርተዋል።
ዕቅዱ በዚሁ በያዝነው ወር በሕግ ይጸናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።
መንግሥት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኙ ኩባንያዎችን ለማዳንም ማቀዱ አልቀረም።
በአንዳንድ የኤኮኖሚ ጠበብት ግምት ይሁንና ዕቅዱ ገቢር ቢሆን ሁኔታውን የማሻሻል ተጽዕኖው ከሚቀጥለው ዓ ም ቀድሞ የሚከሰት አይደለም።
በኢንዲስትሪ ልማት የበለጸጉት መንግሥታት አመለካከትና ፍላጎት በአውሮፓው ሕብረት ውስጥ እንደሚታየው ሁሉ በአሜሪካም የተለየ አይደለም።
ተመራጩ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በሚቀጥለው ሣምንት ሥልጣናቸውን በይፋ ሲረከቡ ግዙፍ የኤኮኖሚ ማነቃቂያ ዕቅዳቸውን ገቢር ማድረግ ይጀምራሉ።
ችግሩን ለመወጣት ከ ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት ለማፍሰስ ያቅዳሉ።
ዕቅዳቸው ታዲያ ከሁሉም በላይ በአገራቸው የሥራ ቦታዎችን በመፍጠርና የሕዝቡን የፍጆት አቅም በማጠናከር የአሜሪካን ኤኮኖሚ ከገባበት አዘቅት ማውጣት ነው።
ብርቱ ፈተና የተደቀነበትን ብሄራዊ ኤኮኖሚ መልሶ የማጠናከሩ ጥረት በመሠረቱ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ባልከፋ
ችግሩ ይህን መሰሉ ዕቅድ የራስን ኤኮኖሚ በማደስ ብቻ ሣይወሰን የመራጭን ድምጽ ለማረጋገጥም የተሰላ እንደሆን ነው።
ይህ ከሆነ ብሄራዊው የኤኮኖሚ ማነቃቂያ ዕቅድ እዚህም ሆነ እዚያ በታዳጊው ዓለም ሕዝብ ትከሻ የሚራመድ እንዳይሆን የሚሰጉት ታዛቢዎች ብዙዎች ናቸው።
በመሆኑም ዕቅዱ ዓለምአቀፍ እንዲሆን የሚሹት የጀርመኑን ግብረ ሰናይ ድርጅት የቴር ዴስ ሆምስን ሥራ አስኪያጅ ፔተር ሙከን የመሳሰሉት ተቺዎች ጥቂቶች አይደሉም።
እንደርሳቸው አባባል ዓለምአቀፉ የኤኮኖሚ ቀውስ ይበልጡን የሚጎዳው ታዳጊዎቹን አገሮች ነው።
እና እነዚህ ሃገራት የውጭ ንግዳቸው በኢንዱስትሪው ዓለም ፍላጎት መቀነስ ስለሚነካ ችግር ላይ ይወድቃሉ።
በመሆኑም ከሁሉም በኢንዱስትሪ ልማት የበለጸጉ አገሮች የሚፈለገው ሌላ ዕርምጃ ነው።
የተሰኘው ዓለምአቀፍ ጸረ ድህነት የተግባር ዘመቻ አመራር ዓባል ሢልቪያ ቦረንና መሰሎቻቸው ሁኔታውን ሞራላዊነት የጎደለው አድርገው ነው የሚመለከቱት።
በወቅቱ እስከ ሚሊያርድ የአሜሪካ ዶላር አራት ትሪሊዮን መሆኑ ነው ባንኮችንና የፊናንሱን ስርዓት ለማዳን እያፈሰስን መሆኑን ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል።
የዚህ ግዙፍ ገንዘብ አንድ ወይም ሁለት በመቶዋ እንኳ የድሃ ድሃ በሆኑት አገሮች ቁጥር ስፍር የሌለውን ሕይወት ለማትረፍ በቻለች ነበር።
እና የፊናንሱን ስርዓት ለማረጋጋት በአንዴ ሰፊ የግብር ገንዘብ ማውጣት እያቻልን ለድሆቹ መርጃ መጥፋቱ ሊያምኑት ያስቸግራል።
የበለጸገው ዓለም የኤኮኖሚ ዕድገት ጥቅም ታች ላሉት እንዳልደረሰ ያለፉት ዓመታት ልምድ አሳይተዋል ባይ ናቸው።
በወቅቱ የፊናንስ ቀውስ የተነሣ ዋነኞቹ የችግሩ ሰለቦች በአብዛኛው ቁዋሚ ሥራ የሌላቸው እዚህም እዚያም እያሉ ለመኖር የሚጥሩት የድሃ ድሃዎቹ ናቸው።
እንደተለመደው የልማት ዕርዳታው ከሁሉም በላይ ለለጋሾቹ ሃገራት ኢንዱስትሪዎች ገበዮችን ከመክፈት ቅድመ ግዴታ ጋር የተሳሰረ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ታዳጊዎቹ አገሮች በ ዓ ም ነዳጅ ዘይት ወደ አገር ለማስገባት ሚሊያርድ ዶላር መክፈል ነበረባቸው።
ራሳቸው ዋና አምራች ካልሆኑ በስተቀር ምግብ ለማስገባትም ከፍተኛ ዋጋ ነው የሚከፍሉት።
አሁን ደግሞ በአሜሪካና በሌሎች ቦታዎች በተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ የተነሣ የውጩን ንግድ ሊገፉበት አልቻሉም።
ስኬት እንዲገኝ ከተፈለገ ዓለም ከብሄራዊ ክልሉ ባሻገር አርቆ ማተኮር መቻል ይኖርበታል።
የታፈነዉ የተቃዉሞና እንቅስቃሴዋ የተቋረጠዉ ጎንደር ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተቃዉሞ ሰልፍ መጠራቱን ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይጠቁማሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ እንቅስቃሴዉ እንደቀዘቀዘ ኅብረተሰቡ ከቤቱ እንደማይወጣ መጓጓዣም እንደሌለ እየተነገረ ነዉ።
አባቶቻችን ጥለዉ ያለፉትን የታሪክ አሻራ እኛ ልጆቻቸዉ በሞያችን እናስተላፍ ብለን ነዉ።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአምቦ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት የከተማዋን ወጣቶች በቁጣ ለተቃውሞ እንዲወጡ ያስገደዳቸው ከውይይቱ በመገፋታቸው ነው ይላሉ።
ውይይቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
በዚህ ውይይት ላይ እንድንካፈል አልተደረገም ያሉት የከተማዋ ወጣቶች ደግሞ ዛሬ ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን የዓይን እማኞች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ውይይቱ እየተካሄደ ባለበት ተመሳሳይ ወቅት ደግሞ በአምቦ ዋና አውራ ጎዳና ላይ የተሰባሰቡ ወጣቶች ተቃውሟቸውን በግልጽ ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
ቄሮ ለምን አልተሳተፈም የሚል ጥያቄ ነበር አስቀድመው ሲጠይቁ የነበረው።
በዚህ ተቃውሞ ላይ ቁጥራቸው ከአስር ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወጥተዋል ብዬ እገምታለሁ እኔ።
ባንኮች ምግብ ቤቶች ሁሉ ዝግ ናቸው ባለው ሁኔታ ኣብይ ሊያስተዳድረን አይችልም የኦሮሞ ልጆችን ጥያቄ መመለስ አይችልም ።
ያኔ ሀገር ቤት የለም ውጭ ይቀመጣል ዛሬ ደግሞ ምን ሊሆን ነው የመጣብን በማለት ነው የወጣነው።
ሌላኛው በተቃውሞው ሰልፍ ላይ የነበረ እና ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገው ወጣት እንዳለው ደግሞ ለተቃውሞ የወጣነው ነጻነታችንን ፍለጋ ነው።
ኮሎኔል መንግስቱንና ፍትህ ኤሜርሶን ማናንጋግዋ አዲሱ መሪ ሆነው ስልጣን መያዛቸው በዚምባብዌ ዜጎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች አፍሪቃውያንም ዘንድ ብሩሕ ተስፋ አሳድሯል።
ምናንጋግዋ የኤኮኖሚዉንና ማህበራዊ ችግር እንደሚያበቁና ወንጀለኞችንም ወደ ፍትህ እንደሚያቀርቡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ከ ዓመት በፊት የቀድሞዉ የዝምባቡዌ ፕሪስዳንት ሮቤርት ሙጋቤ ለኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የፖለቲካ ተገን መስጠታቸዉ ይታወሳል።
የአምነስት ኢንቴርናሽናል ዘገባ እንደሚጠቁመው ኮሎኔል መንግስቱ ዓመት ስልጣን በቆዩበት ወቅት በተለይም በቀይ ሽብር ዘመን ወደ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተገድለዋል።
እንደ ጎርጎረሳዊያኑ በ ዓ ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድቤት ኮሎኔል መንግስቱ በሌሉበት የሞት ቅጣት በይኖባቸዋል።
የዚምባብዌ ባለሥልጣናት መንግስቱን አሳልፈው ይሰጣሉ ብሎ መጠበቅ በጣም የማይመስል ነዉ።
ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ራሳቸውን መከላከል አለባቸው ስሉም አክሎበታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ እንዳለፈዉ መንግስት አምባገነን እና ጨቋኝ እየሆነ መጥቷል።
የዝምባቡዌ የመገናኛ ብዙሃን አዉታሮች የምናንጋግዋ መንግስት መንግስቱን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ እቅድ እንደለለዉ ሰሙኑን ዘግበው ነበር ።
ሆኖም አንድ የጀርመን ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው አዲሱ መንግሥት ኮሎኔል መንግሥቱን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥ አስታውቋል።
የአደጋውን ሰለባዎች የሚያዘክሩ የተለያዩ ዝግጅቶች ከትናንት በስተያ እሁድ ጀምሮ በተለያዩ ስፍራዎች እየተካሄዱ ነው።
ዛሬም በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦች አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ በመገኘት ሙት ዓመቱን አስበዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩል በአብራሪዎች ክበብ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማምሻውን የመታሰቢያ ሥርዓት እያካሄደ ነው።
ዝግጅቱ ይጀመራል ከተባለው ሰዓት ዘግይቶ ሊጀመር አካባቢ በስፍራው የሚገኘውን ዘጋቢያችንን ሰሎሞን ሙጬን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ።
ግን በተቃራኒዉ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ጀምሮ የአሜሪካኖች ወዳጅ ሸሪክ አጋርነታቸዉ የደደረዉ የበርሊን ፓሪስ የሮም ስጳኝ ፖለቲከኞች በዋሽግተኖች መሰለላቸዉ ተጋለጠበት።
ደግሞ በተቃራኒዉ ዋሽግተን ብራስልሶች በጋራ ሶሪያ ላይ የመዘዙትን ሰይፍ ካፎቱ የዶሉበት የግብፅ የዴሞክራሲ ጭላንጭል በመፈንቅለ መንግሥት በዜጎቿ ደም አጥንት የተመረገበት።
ባሜሪካኖች የተሾሙት አሜሪካኖችን ለዓመታት በታማኝነት ያገለገሉት ሐሚድ ካርዛይ የዋሽግተኖችን ትዕዛዝ እንቢኝ ያሉበት ዓመትም ነዉ።
የተለያዩ ከተሞችን ያሸበረዉ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ሰባ ስምንት ሰዎች ገደለ።
ቡሽና ብሌር ያዘመቱት ጦር ባግዳድን ማንደድ የጀመረበት አስረኛ ዓመትን ስትነድ የኖረችዉ ኢራቅ በቦምብ እየነደደች ተቀበለችዉ።
በሽብር እልቂት የጀመረችዉን ዓመት በእልቂት ሽብር ሸኝታ ሌላ ዓመት ልትቀበል ለሌላ እልቂት ሽብር ተሞሽራ ትጠብቃለች።
አፍቃኒስታንም አስራ ሁለት ዓመት እንደኖረችበት ሁለት ሺሕ አስራ ሰወስትን በዉጊያ በዜጎችዋ እልቂት በዘመተባት ጦር አባላት ግድያ ተቀብላ ነዉ የሸኘችዉ።
እና ወደ ረዳቶቻቸዉ ዞር ብለዉ አሜሪካኖች ያሰሯቸዉ ዜጎቼ ያሉበትን ሁኔታ አጣሩሉኝ አሉ አሉ።
የአሜሪካ ጦር ባሰራቸዉ ዜጎቼ ላይ የፈፀመዉን ግፍ እናወግዛለን አሉ፥
አሁን ገዳዮች ለሚሏቸዉ ሲታዘዙ አስራ ሁለት ዓመት ያስቆጠሩት ካርዛይ።
አሜሪካኖች አብዛኛ ጦራቸዉን ካስወጡ በሕዋላ አፍቃኒስታን ሥለሚቆየዉ ጦሯቸዉ ተልዕኮ ያረቀቁትን ስምምነት አልፈርምም አሉ።
የድፍረታቸዉ ድፍረት ቴሕራን ድረስ ሔደዉ ከአሜሪካኖች ቀንደኛ ጠላት ከኢራን ጋር የሠላምና የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።
ከምድር በታች በተከለችዉ የኑክሌር ፋብሪካ ዩራንየም ማንጠር መጀመሯን አስታወቀች።
ኢራን በተደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለዘብተኛ የሚባሉት ፖለቲከኛ ሐሰን ሩሐኒ አሸነፉ።
በኢራን ላይ የተጣለዉን ማዕቀብ ለማስወገድና ለመፍታት ሁለት ጉዳዮችን እንወስዳለን።